ስለ ኮሚሽን መ/ቤቱ




አዲስ አበባ እሳትና አደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን

የእሳትና አደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን የተቋቋመበት ተልዕኮ ማንኛውንም አደጋ መከላከል፣ መቆጣጠርና ሰብዓዊ ዕርዳታ መስጠት ነው፡፡ ይህም ከሌሎች አገልግሎት ሰጭ ተቋማት በተለየ የተቋሙን ሰራተኞች ለአካላዊ፣ አዕምሮኣዊና ስነ-ልቦናዊ ጤና ችግር ተጋላጭ ያደርጋቸዋል፡፡ ሰራተኞች ተጋላጭ የሚሆኑበት አካላዊ፣ አዕምሮኣየና ስነ-ልቦናዊ ችግርም ከእነርሱ አልፎ የቤተሰባቸውን ጤና እና ሰላም የሚያውክ ምጣኔ-ሃብታዊና ማህበራዊ ነው፡፡ ይህም ለተቋሙ ሰራተኞችና ቤተሰቦቻቸው የህክምና አገልግሎት መስጠት እንደሚያስፈልግ ማሳያ ነው፡፡ ኮሚሽን መስሪያ ቤቱም ይህን በመረዳት ክሊኒክ አቋቁሞ ለሰራተኞች የህክምና አገልግሎት ሲሰጥ ቆይቷል፡፡ ከክሊኒኩ አቅም በላይ የሆኑ የጤና ችግሮች የገጥማቸውን ሰራተኞችም ውል ወደ ፈፀመባቸው ሆስፒታሎች ሪፈር በመላክ የተሻለ ህክምና እንዲያገኙ ሲያደርግ ቆዯቷል፡፡ በተጨማሪም በነበረው የህክምና አገልግሎት ሽፋን በቂነት፣ ተደራሽነትና አገልግሎት አሰጣጥ ላይ ሰራተኞች የተለያዩ ቅሬታዎችን ሲያነሱ ቆይተዋል፡፡ በመሆኑም አሰራሩን በቴክኖሎጂ በማገዝ የህክምና ሽፋኑን በማሳደግ የሰራተኞችን እርካታ መጨመር አስፈላጊ በመሆኑ ክለኒኩን የካርድ አወጣጥ የላብራቶሪ አስተዛዘዝ እና የመድሃኒት ኣላላክ ላይ ከወረቀት አሰራር በማለቀቅ አገልግሎቱን ሙሉ በሙሉ በቴክኖሎጂ በማድረግ ክሊኒኩ ቀልጣፋ ውጤታማ እና ፈጣን አገልግሎት ለክሊኒክ ተጠቃሚ መስጠት ነው፡፡

ተግባርና ኃላፊነት

11. የተፈጠሩ ተጎጂዎችና ተፈናቃዮች መጠን የአፋጣኝ መረጃ ትንተና መሰረት በማድረግ በከተማ ደረጃ የአደጋ ጊዜ አስቸኳይ አዋጅ የሚያስፈልጋቸው ሲሆን ለሚመለከተው አካል የውሳኔ ሃሳብ ያቀርባል፤

12. በአደጋ ክስተት ወቅት የሚመለከታቸውን መስሪያ ቤቶችና ነዋሪዎችን በማስተባበር የነፍስ አድን እርዳታን ጨምሮ ፈጣን ምላሽ ይሰጣል፤ በሌላ �ሕግ ለሌላ አካል የተሰጠው ሥልጣንና ተግባር ቢኖርም ለድንገተኛ አደጋዎች የቅድመ ሆስፒታል ህክምና እና አምቡላንስ አገልግሎት ይሰጣል፤

13. መንግስታዊ፣ መንግስታዊ ያልሆኑና የግል ድርጅቶችን እንዲሁም ሌሎች በአስቸኳይ ጊዜ እርዳታ አቅርቦትና መልሶ ማቋቋም ተግባራት ላይ ሚና ያላቸው ተቋማት ያስተባብራል፤

14. የአደጋ ስጋት ስራ አመራር መሰረተ ልማቶችን ከሚመለከታቸው አካላት ጋር በመተባበር ያዘጋጃል፤ ተግባራዊ ያደርጋል፤

15. በአደጋ ምክንያት ከቤት ንብረታቸው የተፈናቀሉ የህብረተሰብ ክፍሎች ጊዜያዊ ድጋፍና መልሶ የማቋቋም ተግባር ያከናውናል፤

16. ለአስቸኳይ ጊዜ እርዳታ አቅርቦት ምላሽ ስራ ብቻ የሚውል የአደጋ ጊዜ ፈንድ፣ ምግብ እና ምግብ ነክ ያልሆኑ ቁሳቁሶች በመጠባበቂያነት ይይዛል፤ ያደራጃል፤ ያስተዳድራል፤ ያሰራጫል፤

17. አደጋ ስጋት ቅነሳ ስራዎች እና በአደጋ ወቅት የአስቸኳይ ጊዜ ምላሽና እርዳታ አቅርቦት አገልግሎቶች ላይ የሚሳተፉ በጎ ፈቃደኞችን ሙያዊ ስልጠና በመስጠት የአደጋ ስጋት ስራ አመራር ተግባራት ላይ ተባባሪ እንዲሆኑ ይሰራል፤

18. በአደጋ ስራ አመራር ሥርዓት ውስጥ ተሳታፊ በሚሆኑ ባለድርሻ አካላት መካከል ቅንጅታዊ አሰራርን ለማስፈንና ውጤታማነታቸውን ለማረጋገጥ የጋራ መድረኮች ይመሰርታል፤ ያስተባብራል፤

19. አደጋ በይፋ መገለጹን ተከትሎ ሲወሰን ከተለያዩ አካላት ለምላሽ ስራ የሚውል ሀብት ያሰባስባል፤

20. የኮሚሽኑን ፓራ ሚሊተሪ ሰራተኞችን ካቢኔ በሚያወጣው ደንብ መሠረት ይቀጥራል፤ ያስተዳድራል፡፡

1. የመረጃና ቴክኖሎጂ ማዕከል በማቋቋም ከአደጋ በፊትም ሆነ በአደጋ ጊዜ እና በኃላ የተማከለ የመረጃ ልውውጥ ስርዓት እንዲኖር ያደርጋል፣ በከተማ ደረጃ የአደጋ ስጋት ስራ አመራር የመረጃ ማዕከል ሆኖ ያገለግላል፤

2. የተፈጥሮና ሰው ሰራሽ አደጋዎች መንስኤና የተጋላጭነት ደረጃና ትንተና መረጃ ያሰባስባል፤ የቅድመ አደጋ ጠቋሚ ጥናቶችን በማካሄድ አስፈላጊውን የቅድመ ማስጠንቀቂያ እርምጃዎችን ይወስዳል፤ እንዲወሰው ያደርጋል፤ ይከታተላል፤

3. በሰው ሰራሽም ሆነ በተፈጥሮ ሊከሰት የሚችል አደጋን የመከላከል እና የአደጋ ጉዳት ቅነሳና የማጣጣም ስራን ይሰራል፤ ሌሎች ተቋማትም እንዲሰሩ ያደርጋል፤

4. በከተማዋ የሚገኙ ተቋማት የአደጋ ስጋት ቅነሳ እቅድን በልማት እቅዶቻቸው ውስጥ እንዲያካትቱ ያደርጋል፤ ተግባራዊ እንዲሆኑ ይከታተላል፤

5. የተቋሙ ባለሙያዎች፣ ልዩ ልዩ ተቋማትና ህብረተሰቡ ስለ አደጋ ስራ አመራር ስልጠና የሚያገኙበት የስልጠና ማእከል ያደራጃል፤

6. በተከታታይ ወይም በዕቅድ ላይ ተመስርቶ የናሙና ልምምዶች ያከናውናል፤ እንዲከናወኑም ሁኔታዎችን ያመቻቻል፤ በአደጋ ምላሽ እቅድ ላይ የማስተካከያ እርምጃ ይወስዳል፤ እንዲወሰድ ያደርጋል፤

7. የአደጋ መከላከያና መቆጣጠሪያ መሳሪዪችን፣ የአደጋ ጊዜ ማምለጫ ደረጃዎች፣ የእሳትና የጭስ፣ የነበልባል እና ሌሎች አደጋ ጠቋሚ መሳሪዪች በአገልግሎት መስጫ ልዩ ልዩ ተቋማት መተከላቸውንና በአግባቡ መስራታቸውን ይከታተላል፤ ይቆጣጠራል፤ እርምጃ ይወስዳል፤ እንዲወሰድ ያደርጋል፤

8. ወቅታዊና ትክክለኛ መረጃ ለህዝቡ ለማድረስ ሁሉን አቀፍ የቅድመ አደጋ ማስጠንቀቂያ ስርዓት ሥራ ላይ እንዲውል ያደርጋል፤ ለህብረተሰቡ የቅድመ አደጋ ማስጠንቀቂያ መረጃዎችን፤ በአደጋ ወቅት መውሰው ያለባቸውን እርምጃዎች እና የደረሰውን አደጋ በተመለከተ ወቅታዊ መረጃዎችን የማሰራጨት ተግባር ያከናውናል፤

9. በአደጋ የተጎዱና የተፈናቀሉ አካላት የአጠቃላይ የጉዳት መጠን፣ ክስረትና ፍላጎት መረጃ በማሰባሰብ ይተነትናል፤ ያደራጃል፤ ለሚመለከተው አካል የውሳኔ ሀሳብ ያቀርባል፤ ሲወሰንም ተከታትሎ ይፈጽማል፤ ያስፈጽማል፤

10. በከተማው የአደጋ ተጎጂዎችና ተፈናቃዮች ወቅታዊና ተደራሽ የሆነ የአደጋ ምላሽና መልሶ ማቋቋም የአደጋ ምላሽ አሰጣጥ ስራ አመራር ስርዓት ይዘረጋል፤

የኮሚሽን መ/ቤት አድራሻ:

ፒያሳ

ስልክ ቁጥር:

+251118223344

Loading
Your message has been sent. Thank you!